“ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” ፤ እግዚአብሔር ለሚሠራው ሥራ ጊዜ አለው።መዝ ፻፲፰÷፻፳፬-፻፳፮ለአመታት በተለያዩ የምስረታ ሂደቶች ውስጥ ያለፈው የሐመረ ብርሀን ቅዱስ አብነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ገዳም እንደ እግዚአብሔር ቸርነትና ፈቃድ የብድርና የቦታ ግዢ ኩነቶችን በማጠናቀቅ የገዳሙን ምስረታ እውን አድርግዋል። የገዳሙ የምስረታ አባላት ኮሚቴ ከረጅም ጊዜ ያላሰለሰ ጥረትና ልፋት በኅዋላ ትላንት ሰኔ 17 2014 ዓ.ም በፃድቁ አምላክ ቸርነት የገዳሙን የግዢ ውል ስምምነት አጠናቆ ቦታውን ከሻጭ ላይ ተረክብዋል። በመንገዳችን ቀድሞ የረዳንን ፤ ስንደክም ያበረታንን ፤ ተስፋ ስንቆርጥ ያፅናናንን ፤ የልባችንን ሀሳብ የፈፀመልንን የአምላካችን ስም ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን። ከመነሻ ፅንሰ ሀሳብ ጀምሮ በፀሎት፤ በሀሳብ ፤ በገንዘብ ድጋፋችሁ ስላልተለየን በፃድቁ ስም ክብረት ይስጥልን። በተለያዩ የምስረታ ኮሚቴዎች ውስጥ በሱታፌ ያገለገላችሁ ጠቢብ በሆነው መንገዱ ተስፋ አስቆራጭ የነበሩ ሁነቶችን አሳልፎ ብርታትና ጉልበት ሆኖን የልፋታችሁን በረከት ስላያችሁ እንኳዋን ደስ አላችሁ። አብሮን የቆየ አንድነታችሁና እገዛችሁ እንደማይልየን በማመን በቀጣይ በገዳሙ ሊሰሩ የታቀዱ እቅጣጫ የተቀመጠባቸው የስራ ሂደቶችን ለምእመናን በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል።ወስብሀት ለእግዚአብሄርከገዳሙ ጵህፈት ቤትHamere Berhan St Abba Samuel EOTM has acquired a new property located at 18429 Youngs Ln, Elkwood, VA 22718 and the purchase agreement signed and received the key yesterday June 24,2022. We Praise the Lord!