Great Lent Seventh Sunday Nicodemus ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛው ሳምንት)
ሰባተኛው ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ› የሚል ስያሜ ያለው ሲኾን፣ የስያሜው መነሻም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ የተመዘገበው ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ አለቃ ታሪክ ነው፡፡ ኒቆዲሞስ በሦስት መንገድ የአይሁድ አለቃ ነበር፤ በሥልጣን፣ በዕውቀትና በሀብት፡፡ ሰው ሥልጣን ቢኖረው ሀብትና ዕውቀት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ላይኖረው ይችላል፡፡ ሀብት ቢኖረውም ዕውቀትና ሥልጣን ላይኖረው ይችላል፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ሦስቱንም አንድ ላይ አስተባብሮ የያዘ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ወንጌልን ለመማር ከአይሁድ ዅሉ ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ይሔድ ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ፈሪሳውያን ማመን ባልቻሉበት በዚያን ዘመን ጆሮውን ለቃለ እግዚአብሔር፤ ልቡን ለእምነት የከፈተ ሰው ነው፡፡ ብዙ ሰዎችን እናውቃለን ማለት ከመልካም ነገር ሲከለክላቸው ኒቆዲሞስ ግን ዐዋቂ ሳለ ራሱን ዝቅ አድርጎ፣ እምነት በማጣት የነጠፈችውን የፈሪሳውያንን ኅብረት ጥሎ፣ ሐዋርያትን መስሎ ጌታውን አግኝቶታል፡፡ ጌታችን ዓለምን ለማዳን ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በለየባት በዚያች አስጨናቂ ሰዓት፤ ሐዋርያት በተበተኑባት አይሁድ በሠለጠኑባት በዕለተ ዓርብ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን በድርብ በፍታ ገንዞ የቀበረ፣ እሱን ያገኘ ያገኘኛል ሳይል በድፍረት ከእግረ መስቀሉ የተገኘ ሰው ነው – ኒቆዲሞስ፡፡ ስለዚህም ሰባተኛው ሳምንት በእርሱ ስም ተሰይሟል፡፡
በዘመነ ሥጋዌ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምደር መምጣትና መሲሕ መባል ያልተቀበሉት በርካታ እስራኤላዊያን እርሱን እስከመስቀል እንደደረሱ ወንጌል አስተምሮናል፡፡ ሆኖም በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው ከተከተሉት ፈሪሳውያን አንዱ ኒቆዲሞስ ለታላቅ ክብር የበቃ ሰው ሆኗል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህን ታላቅ ሰው ለመዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሑድ በስሙ ሰይማ ታከብረዋለች፤ ተከታዮቿ ምእመናንም የእርሱን አሠረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች፤ ታስተምራለችም፡፡
ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ያመነ የተጠመቀ ይድናል፡፡ ያላመነ ያልተጠመቀ ግን ይፈረድበታል፤››(ማር.፲፮፥፮) በማለት በሰጠን ቃል ኪዳን መሠረት በአምላክነቱ አምነን የመንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ ይፍቀድልን፤ ለኒቆዲሞስ ምሥጢሩን እንደ ገለጸ ለእኛም ይግለጽልን፤ አሜን፡፡
ምንባባት
መልዕክታት
ሮሜ ምዕራፍ 7÷1-19
1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ 4: 10- ፍጻሜው
ግብረ ሐዋርያት :- ሐዋ. 5÷34 – ፍጻሜው
ምስባክ:- መዝ.16÷3
ሐውጽከኒ ሌሊት ወፈተንኮ ለልብየ፥ አመከርከኒ ወኢተረክበ አመጻ በላዕሌየ፤ ከመ ኢያንብብ አፍየ ግብረ ዕጓለእመሕያው
ትርጉም፦ ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም። የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤
ወንጌል :- ዮሐንስ 3÷1-20
ቅዳሴ: – ዘእግዚትነ
The Seventh Sunday Nicodemus: A ruler of the Jews Reading
Saint John 3: 1 – 13
The theme in the seventh Sunday in the Great Fast points to the new birth given by water and the Holy Spirit. Nicodemus a ruler of the Jews came to our Lord by night seeking to escape the world of darkness and sin because he saw in Christ the light of salvation and life. Our Lord did not reject him but received him with Heavenly instructions. He explained to Nicodemus the preconditions of salvation in the Kingdom of God exists only if he believed that He was the God’s own Son and that he was equal with God the Father and that the power to become children of God by rebirth is available only through the mystery of Baptism, which is one of the seven Sacraments of the Church.
Nicodemus was a leader of the Jews who came to our LORD by night seeking knowledge; He wanted to ask questions for saw Christ the light of salvation and life. Our LORD did not reject him but received him; and even explained to Nicodemus the way to salvation and inheritance of the Kingdom of God. He thought about faith, becoming God’s own Son and the Mystery of Trinity leading of becoming children of God by rebirth through the Mystery of Baptism.
To be baptized into the divinity of Christ, we are entering a covenant, which “fulfills all righteousness.” It is beyond our capability to understand this great mystery of God’s condescending love to save us_ even if we live to be as old as Nicodemus and earn Ph.D.’s in Theology. Yet, we can know from what He has revealed, that this opening of the font of grace is vital to our eternal life. It is an initiation, like circumcision was in the covenant which God made with Abraham, telling him that he, all of his household, and all of his children must be initiated. From Apostolic times whole households were, also, baptized into Christ.
Readings:
Romans 7: 1-19
1 John 4: 18 – finish
Acts 5: 34- finish
Psalm 16:3
Though you probe my heart, though you examine me at night and test me, you will find that I have planned no evil; my mouth has not transgressed
John 3: 1 – 20
Liturgy: Anaphora of St. Mary